Saturday, August 6, 2011

በሳያት ደምሴ የአትላንታ ኮንሰርት ምክንያት የተቋረጠው ታዲያስ አዲስ ተጀመረ
በሰይፉ ፋንታሁን የሚመራው እና በሳምንት አምስት ቀናት ለአየር የሚበቃው የታዲያስ አዲስ ፕሮግራም እንደገና ተጀምሯል፡፡ፕሮግራሙ ሳያት በአትላንታ ባቀረበችው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በሰነዘረው ትችት ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን የፕሮግራሙ አዘጋጆች ከ ሸገር 102.1 የስራ ሃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ እንደተጀመረ ታውቋል፡፡የአውራምባ ታይምስ የቅዳሜ እትም የፕሮግራሙን መጀመር የዘገበ ሲሆን ጋዜጣው አለመግባባት በፈጠረው ትችት ዙሪያ የጣቢያው ሃላፊዎች አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አትቷል፡፡የፕሮግራሙ አዘጋጅ ተወልደ በየነ(ተቦርነ) በበቂ መረጃ ላይ ተመርኩዘው ትችቱን ማቅረባቸውን እና ሳያት ደምሴ ቅሬታ ካላት ጉዳዩን ወደ ህግ መውሰድ እንደሚኖርባት ተናግሯል፡፡ሰይፉ ፋንታሁን ከታዲያስ አዲስ በፊት በኤፍኤም አዲስ 97.1 አዲስ ዜማ የተሰኘ የመዝናኛ ፕሮግራም ያዘጋጅ ነበር፡፡በሳያት ደምሴ ላይ በተሰነዘረው ትችት ምክንያት የፕሮግራሙ መቋረጥ በአዲስ አበባ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቆይቷል፡፡  

No comments:

Post a Comment